ሰነድ ማረጋገጥ/ ውክልና

በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት (አዋጅ ቁጥር 95/2015) ሰነድ ማረጋገጥ “ማለት አዲስ ሰነድ በአዘጋጁ ወይም ጉዳዩ በሚመለከተው ሰው ሲፈረም ማየትና ይኸው መፈፀሙን በማረጋገጥ በሰነዱ ላይ መፈረምና ማኅተም ማድረግ ወይም አስቀድሞ በተፈረመ ሰነድ ላይ የሚገኝ ፊርማንና ወይም ማኅተምን በቃለ መሀላ ወይም ማኅተም ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ በሰነዱ ላይ መፈረምና ማኅተም ማድረግ ነው።”

በዚህ ክፍል የሚሰጠው የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት አዲስ ሰነድ በአዘጋጁ ወይም ጉዳዩ በሚመለከተው ሰው ሲፈረም ማየትና ይኸው መፈፀሙን በማረጋገጥ ቆንስላ ጽ/ቤቱ በሰነዱ ላይ በመፈረምና ማኅተም በማድረግ የሚሰጥ አገልግሎት ይመለከታል።

አገልግሎቱ በቆንስላ ጽ/ቤቱ በአካል በመቅረብ ለማግኘት ከስር የተዘረዘሩትን አሟልተው ይምጡ።

  • በሶስት ኮፒ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ወይም መሻሪያ፣ ውል፣ ኑዛዜ፣ ቃለ ጉባኤ፣ የማህበራት መመስረቻ ፅሁፍ ወይም መተዳደደሪያ ደንብ፣ እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰነዶች
  • ተሞልቶ የተፈረመ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ (ቅጹን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ)
  • የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት እና የአሜሪካን አገር የመኖሪያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ)፣ የስራ ፍቃድ ወይም ነዋሪ ላልሆኑ I 94 ኮፒ
  • የውጭ አገር ፓስፖርት ወይም የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ

የአገልግሎት ክፍያ

            $62.00 በሰነድ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ

            $95.00 በሰነድ የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት ለያዙ

የአገልገሎት ክፍያ መፈጸም የሚቻለው ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ተከፋይ እንዲሆን በተዘጋጀ በመኒ ኦርደር ወይም ካሸር ቼክ ብቻ ነው።

ማስታወሻ

አገልግሎቱን በ20 ደቂቃ ውስጥ ይሰጣል።