የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት

ሰነድ ማረጋገጥ

በኢትዮጵያ ህግ መሰረት (አዋጅ ቁጥር 95/2015) ሰነድ ማረጋገጥ ማለት “አዲስ ሰነድ በአዘጋጁ ወይም ጉዳዩ በሚመለከተው ሰው ሲፈረም ማየትና ይኸው መፈፀሙን በማረጋገጥ በሰነዱ ላይ መፈረምና ማኅተም ማድረግ ወይም አስቀድሞ በተፈረመ ሰነድ ላይ የሚገኝ ፊርማንና ወይም ማኅተምን በቃለ መሀላ ወይም ማኅተም ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ በሰነዱ ላይ መፈረምና ማኅተም ማድረግ ነው።”

ይህ ክፍል አስቀድሞ በተፈረመ ሰነድ ላይ የሚገኝ ፊርማንና ወይም ማኅተምን በቃለ መሀላ ወይም ማኅተም ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ የቆንስላ ጽ/ቤቱ በሰነዱ ላይ በመፈረምና ማኅተም በማድረግ የሚሰጥ አገልግሎት ይመለከታል።

እባክዎ ለአዲስ ውክልና ስልጣን ማስረጃ ወይም መሻሪያ ፣ውል፣ ኑዛዜ፣ቃለ ጉባኤ፣የማሕበራት መመስረቻ ፅሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰነዶች በቆንስላ ኦፊሰር ፊት በመፈረም የሚሰጠውን የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት ውክልና የሚለውን ክፍል ይጎብኙ።

ሰነድ ማረጋገጥ መስፈርቶች

  • ከአሜሪካ አገር የመነጨ ሰነድ በቅድሚያ ሰነዱ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው በስቴት ዲፓርትመንት (የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል። ለተጨማሪ መረጃ የስቴት ዲፓርትመንትን ድረ ገፅ ይመልከቱ
  • ከኢትዮጵያ የመነጨ ሰነድ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርበታል
  • ተሞልቶ የተፈረመ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ (ቅጹን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ)
  • የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት እና የአሜሪካን አገር የመኖሪያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ)፣ የስራ ፍቃድ ወይም ነዋሪ ላልሆኑ I 94 ኮፒ
  • የውጭ አገር ፓስፖርት ወይም የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ

በፖስታ የሚቀርቡ የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት

  • በፖስታ ለሚቀርቡ የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ከላይ የተገለጹትን መስፈርት በማሟላት፣ ሰነዱ ተሰርቶ የሚላክበት የተከፈለበት፣ የመከታተያ ቁጥር እና አድራሻ የተፃፈበት ፖስታ ማያያዝ ይኖርቦታል።

የአገልገሎት ክፍያ

  • ለትምህርትና ሙያ ምስክር ወረቀት ወይም ዲፕሎማ ወይም የወሳኝ ኩነት ሰነዶች (የልደት፣ የጋብቻ፣የፍቺ፣ የሞት፣ ከጋብቻ ነፃ ምስክር ወረቀት) ወይም የንግድ ምልክት፣ የንብረት ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ ፣ የመንጃ ፍቃድ ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ሰነዶች፡-

$59.00 በሰነድ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ

$90.00 በሰነድ የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት ለያዙ

  • ለውክልና ስልጣን ማስረጃ ወይም መሻሪያ ፣ ውል፣ ኑዛዜ፣ ቃለ ጉባኤ፣ የማህበራት መመስረቻ ፅሁፍ ወይም መተዳደደሪያ ደንብ፣ እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰነዶች፡-

$62.00 በሰነድ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ

$95.00 በሰነድ የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት ለያዙ

የአገልገሎት ክፍያ መፈጸም የሚቻለው ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ተከፋይ እንዲሆን በተዘጋጀ በመኒ ኦርደር ወይም ካሸር ቼክ ብቻ ነው።

ማስታወሻ

  • በአካል ቀርበው የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ለሚጠይቁ በ20 ደቂቃ በፖስታ ለሚላኩ የአገልግሎት ጥያቄዎች ሰነዱ ለቆንስላ ጽ/ቤት በደረሰ በሁለት የስራ ቀናት ውስጥ አገልግሎት ያገኛሉ።