ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች

  • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፣
  • አምስት አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርቦታል፣
  • በአምስት አመት ውስጥ ከአንድ ግዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም፣
  • አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች እባክዎ መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን። (Click here to download the Form)
  • የንብረቶች ዝርዝር በዚህ ፎርማት ያቀረቡ (Leave for good items )

የፖስታ አላላክ መመሪያ

  • በፖስታ ቤት አማካኝነት አገልግሎቱን የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው(UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL) መሆን ይገባዋል፡፡
  • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡
  • ማመልከቻዎ ኤምባሲው ከተረከበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታTracking Number በመጠቀም ያጣሩ!