የውክልና አገልግሎት

የውክልና እና የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ
እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ይላኩ።
 • እንዲረጋገጥልዎ የፈለጉት የውክልና ሰነድ ሆኖ ኢትዮጵያዊ/ት ሆነው የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ ፓስፖርት ወይም ያገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ካለዎት የውክልና ሰነዱን ኖተራይዝ አስደርገው ከሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በቀጥታ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት መላክ ይችላሉ። ነገር ግን አገልግሎቱ የፀና የትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት ውክልናውን በአማርኛና በእንግሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊስ ቀጥሎ ዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት ከተረጋገጠ በሁዋላ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን መላክ ይኖርብዎታል።
 • ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚቀርብ ዶክመንት ከአሜሪካን መንግስት የመነጨ (የተሰጠ) ከሆነ (ለምሳሌ – ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣  የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ካሉበት አካባቢ ስቴት ኦፊስ በመሄድ ዶኩመንቱን ካረጋገጡ በኋላ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርበታል።
 • ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።
 • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን
  ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ መደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት መደወል አይጠበቅብዎትም።
1. የውክልና አገልግሎቶች

ሀ. የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው እና የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ የውጭ ሀገር ዜጎች

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 ኖተራይዝ የተደረገ ውክልና መላክ ወይም ኖተራይዝ ሳያስደረጉ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን በአካል ቀርቦ ውክና ማስፈፃም ይችላሉ።
2 በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆኑ የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ ፤ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ካለዎት የታደሰ የመታወቂያ ካርድ ኮፒ
3 በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆኑ በአሜሪካን አገር የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የግሪን ካርድ  ወይም ግሪን ካርድ ከሌለዎት የ  I – 94 ወይም የስራ ፍቃድ ማስረጃ ኮፒ
4 የአገልግሎት ክፍያ $62.00 ዶላር ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/
 5 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (Click here to download a Form)
6 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
 
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
ለ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ለሌላቸው ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 ያዘጋጁቱን ውክልና በመጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊስ ቀጥሎ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት አረጋግጦ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን
መላክ፣
2 የአገልግሎት ክፍያ $95.00 ዶላር ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/፣
3 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት(Click here to download a Form)፣
4 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
2.  የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ

ሀ. ከአሜሪካን መንግስት ለተሰጡ የተለያዩ ዶክመንቶችን ለማረጋገጥ

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 ሰነዱን መጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊስ በማረጋገጥ በመቀጠል ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት አረጋግጦ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን መላክ፣
2 የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ ሆኖ የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ  ኮፒ ካያያዙ $60.00 ዶላር ሲሆን የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት $95.00 ዶላር ነው፡፡
3 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download a form)
4 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
 ለ. በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 መጀመሪያ ለማረጋገጥ የሚፈለገው ዶክመንት በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል
2 የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ ሆኖ የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ  ኮፒ ካያያዙ $60.00 ዶላር ሲሆን የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት $95.00 ዶላር ነው፡፡
3 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download a form)
4.            አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣

ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

አገልግሎቱ የሚፈጅበት ጊዜ

ለሁሉም ዶኩመንት ለማረጋገጥ
 • በአካል ቀርበው ለሚያስፈፅሙ በ24 ሰዓት ውስጥ
 • በመልዕክት /mail/ ለሚልኩ ማመልከቻው ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ በ48ሰዓት ተጠናቅቆ ይላካል፣
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ቅጾች /ፎርሞች/
1.      የማመልከቻ ቅጽ   (click here to download a form)