የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት

ETHIOPIAN ORIGIN ID

1.  የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አሠጣጥ 

የኢትዮጵጵያ ተወላጅነት መታወቂ ካርድ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

1.1.    የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጠው የሚያመለክት የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ፡-

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-

 • መታወቂያውን ለማግኘት ዜግነት ከወሰደበት አገር የተሠጠውና አገልግሎቱ ቢያንስ ለስድስት ወራት የፀና ፓስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል። ከላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ከሚከተሉት አንዱን ሙሉ ስም ከነአያት የሚገልጽ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር የሰነድ ማስረጃ በተጨማሪ ማቅረብ አለበት። ሆኖም ግን በአንዳንድ አገሮች እና በቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በሁለት ስም ብቻ የሚገለጽ ስለሆነ ይህንኑ ተቀብሎ ማስተናገድ ይቻላል። በፓስፖርት ላይ ያሉ ስሞችንም ይመለከታል። ይህም የሚቻለው ስም ከነአያት የሚገልጽ ሌላ ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃ ሲያቀርብ  ነው፡፡
 • የአመልካቹ አግባብ ካለው አካል የተሰጠና የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር፣ ወይም፣
 •  የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር  ወይም፣
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ከነበሩ የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ፣ ወይም፣
 • ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋግጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉድፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ፣ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ፣ ወይም፣ ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠ እና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ ፣ ወይም፣
 • ሥልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም አያቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ ፣

ከላይ ከተመለከቱት ውስጥ አንዱንና ቀጥሎ የተመለከቱትን ማለትም፡-

 • ማንኛውም አመልካች የጣት አሻራ በሀገር ውስጥ በኢሚግሬሽን፣ በውጭ አገር ሲሆን በሚሲዮን ጽ/ቤት ወይም በአካባቢው በሚገኝ የፖሊስ ጽ/ቤት አሻራ የሰጠበት ሰነድ ሲቀርብ፣
 • ሶስት በቅርብ ጊዜ የተነሳው ሙሉ ፊቱን የሚያሳይ ሶስት በአራት ሴ.ሜ የሆነ ፎቶግራፍ፣ እና
 • ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት በሁለት ቅጅ ሲያቀርብና፤
 • ጥያቄ የቀረበለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን በጥያቄው መሠረት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት አመልካቹ የማይመለከቱት መሆኑን ሲረጋገጥ ለአምስት ዓመት የሚያገለግል የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲያገኝ ይፈቀድለታል፣ መጠየቂያ ፎርሙን እዚህ ተጭነው ይመልከቱ  (click here to download)
 • የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click here to download Fingerprint Capture FORM)
 • ስት (3)  የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
 • የአገልግሎት ክፍያ 200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
 •  መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
 • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
 • አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL)ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

1.2.    አካለ መጠን ላላደረሰ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጅ ስለሚሰጥ አገልግሎት

 መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-

ዕድሜው 18 ዓመት ያልሞላው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የተቀበለ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው ልጅ የግሉ መታወቂያ ማውጣት ሳይገደድ በወላጅ አማካይነት የሚከተሉት ሲሟሉ :-

 • የልጁ ፖስፖርት ቢያንስ ለስድስት ወር አገልግሎቱ የፀና ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር፤
 •  የልጁ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠና ህጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር፤
 • የወላጅ አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር፤
 • ልጁ በቅርብ ጊዜ የተነሳው ሙሉ ፊትን የሚያሳይ 3 ጉርድ ፎቶግራፍ ከሁለት ማመልከቻ ቅጽ ጋር በማያያዝ፤
 • ዕድሜው 14 ዓመት እና ከ14 ዓመት በላይ የሆነውና 18 ዓመት ያልሞላው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የተቀበለ የውጭ አገር ልጅ የጣት አሻራ ሰጥቶ ከኢትዮጵያ ውጭ ሲሆን በሚኖርበት አገር ለተወከለው የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሚሲዮን ሲያቀርብ፤
 • የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጅ እድሜው ለአካለ መጠን ሲደርስ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 4 መሠረት በራሱ ጠያቂነት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ መስፈርትን ሲያሟላ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲሰጠው ይደረጋል።
 • ዕድሜው 18 ዓመት ያልሞላው በዚህ መመሪያ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ አገር ዜጋን ትርጓሜ የሚያሟላ ማንኛውም ሰው በወላጅ ወይም በአሳዳጊ አመልካችነት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ሲያሟላ፡- በተጨማሪም
 • ዕድሜው 14 ዓመት እና ከ14 ዓመት በላይ የሆነውና 18 ዓመት ያልሞላው ልጅ የጣት አሻራ ሲሰጥ ለአምስት ዓመት የሚያገለግል የግሉ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲያገኝ ይፈቀድለታል።

1.3. ለኢትዮጵያ ተወላጅ የትዳር ጓደኛ ስለሚሰጥ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ:-

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-

 • የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ያለው/ያላት ያገባች/ ያገባ የውጭ አገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዕድገትና ብልጽግና የበኩሉን/ሏን አስተዋጽኦ ያበረክታል/ታበረክታለች ተብሎ ከታመነ ቀጥሎ የተመለከቱትን በማሟላት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ሊሰጠው/ሊሰጣት ይችላል፣
 • መታወቂያውን ለማግኘት ዜግነት ከወሰደችበት /ከወሰደበት አገር የተሰጣትን/ የተሰጠውን አገልግሎቱ ቢያንስ ለስድስት ወር የፀና ፖስፖርት፣ በአንዳንድ አገሮች ሁለት ስም ስለሚገለፅ ይህንኑ ተቀብሎ ማስተናገድ ይቻላል፤
 • ቢያንስ ሁለት (2) ዓመት የሆነው የተረጋገጠ የጋብቻ ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅ ጋር ፣
 • የባል/የሚስት አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናውን ከሁለት ቅጅ ጋር ፣
 • የትዳር ጓደኛው/ዋ በቅርብ ጊዜ የተነሳውን/የተነሳችውን ሶስት የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍና፣
 • መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ የጸና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ ፣
 • ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀው የማመልከቻ ቅጽ ሞልቶ ከሁለት ቅጅ ጋር በማያያዝ ከአገር ውጭ ሲሆን ለኢትዮጵያ ሚሲዮን በአገር ውስጥ ሲሆን ለኢሚግሬሽን ያቀርባል፣
 • በመመሪያው አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 4.3.1 መሠረት የጣት አሻራ ሲሰጥ፤
 • ጥያቄ የቀረበለት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን ወይም ኢሚግሬሽን ለጥያቄው ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት አመልካቿ/አመልካቹ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 የተዘረዘሩት ሁኔታዎች የማይመለከቷት /የማይመለከቱት መሆኑን ሲረጋገጥ ለ5 ዓመት የሚያገለግል የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ አገር ዜጋ ሚስት/ባል መሆኑን ወይም መሆንዋን የሚገልጽ የመታወቂያ ካርድ እንድታገኝ/እንዲያገኝ ይፈቀዳል።
 • መጠየቂያ ቅጽ-2 በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)
 • መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ ነው፡፡ (Click here to download the form)

o   የአገልግሎት ክፍያ 200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ

  • መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም
  • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
  • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/

o   አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣

ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

1.4. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት

የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት አገልግሎት የሚሰጠው ቀጥሎ የተመለከቱትን በማሟላት ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን ወይም ለኢሚግሬሽን ሲቀርብ ነው፣

 •  ዜግነት ካገኘበት አገር የተሰጠውና ቢያንስ ለስድስት ወር አገልግሎቱ የፀና ፖስፖርት ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር፤
 • ቀደም ሲል የተሰጠው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር፤
 • በቅርብ ጊዜ የተነሳው ሙሉ ፊትን የሚያሳይ ሦስት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፤
 • የጣት አሻራ በአገር ውስጥ በኢሚግሬሽን፣ በውጭ አገር ሲሆን በሚሲዮን ጽ/ቤት ወይም በአካባቢው በሚገኝ የፖሊስ ጽ/ቤት አሻራ የሰጠበት ሰነድ፤
 • በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ፤
 • የእድሳት ማመልከቻ በሁለት ቅጅ ተሞልቶ ሲቀርብ፤
 • የእድሳት ጥያቄ የቀረበለት የኢፌዲሪ ሚሲዮን ወይም ኢሚግሬሽን ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት አመልካቹ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 ስር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች የማይመለከቱት መሆኑን ሲረጋገጥና፤
 • ተገቢው ክፍያ ሲፈፀም መታወቂያው ለ5 ዓመት እንዲታደስለት ይፈቀድለታል።
 • በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download the form) ተያይዞ ሲቀርብ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 • የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻር መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click here to download Fingerprint Capture FORM)  ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅቦትም፡፡
 • የአገልግሎት ክፍያ 200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
 • መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም
 • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
 • አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL)ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

1.5.  የጠፋ ወይም የተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ስለ መተካት

 •  ለጠፋ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ምትክ ሊሰጥ የሚችለው መታወቂያው ስለመጥፋቱ ለአካባቢው ፖሊስ ወይም አግባብ ላለው አካል ያመለከተ ለመሆኑ በቂ የሆነ ማስረጃ ሲቀርብና የጠፋው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዝርዝር መረጃ ለሚሲዮን ወይም ለኢሚግሬሽን ሲቀርብ ነው። ሚሲዮኑ ባለበት እና በተወከለባቸው ሀገሮች ከአካባቢው ፖሊስ መታወቂያ ካርዱ ስለመጥፋቱ ሪፖርት ስለማድረጉ ማስረጃ እንደማይሰጥ ሚሲዬኑ ካረጋገጠ አመልካቹ መታወቂያው ስለመጥፋቱ የሚያቀርበው ማመልከቻ ቢሚሲዮኑ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
 • የጠፋው ወይም የተበላሸው መታወቂያ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ በሁለት ቅጅ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ፣
 • የጠፋው ወይም የተበላሸው መታወቂያ ካርድ ከሆነ አገልግሎቱ የፀና የወላጅ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ፤
 • የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እንዲተካ ጥያቄ የቀረበው በመጀመሪያ መታወቂያዉን ከሰጠው አካል ውጭ ከሆነ ጥያቄው የቀረበለት የኢትዮጵያ ሚስዮን ወይም ኢሚግሬሽን የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ መጀመሪያ የሰጠውን አካል እንደአስፈላጊነቱ መረጃና በጥያቄው ላይ ያለውን አስተያየት መጠየቅ ይኖርበታል::
 • የጠፋው ወይም የተበላሸው መታወቂያ ካርድ ከሆነ የሚተካው መታወቂያ ካርዱ የአገልግሎት ዘመን 5 አመት ሲሆን የልጁ ዕድሜ 18 ዓመት እስካልሞላው ድረስ ይሆናል፤
 • አመልካች የጠፋ ወይም የተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ሲተካ የሚጠየቀውን ክፍያ እንዲከፍል ይደረጋል።
 • አሻራ ያልሰጡ ዕድሜአቸው 14 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው አመልካቾች ሁሉ አሻራ እንዲሰጡ ይደረጋ።
 • መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)
 • መታወቂያው ስለመጥፋቱ በግለሰቡ የተፃፈ ማመልከቻ
 • የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ
 • የቀድሞ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ (የመታወቂያው ኮፒ ከሌለዎት መቼ እና ከየት እንደወሰዱት የሚገልፅ ማስታወሻ አያይዘው ይላኩ)
 • የጠፋው መታወቂያ ካርድ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download the form) በሁለት ቅጅ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 • የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻር መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click here to download Fingerprint Capture FORM) ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅቦትም፡፡
 • ሶስት (3)  የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)

የአገልግሎት ክፍያ

 • በጠፋ ምትክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰጥ ከ 18 አመት በላይ ለሆኑ 240ዶላር፤
 • በጠፋ ምትክ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሰጥ ከ 18 አመት በላይ ለሆኑ 300 ዶላር፤
 • በጠፋ ምትክ ለሶሰተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ ሲሰጥ ከ 18 አመት በላይ ለሆኑ 400 ዶላር፤
 • ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
  • መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም
  • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
  • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
 • አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

 

1.6.   የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እርማት፤

 •  የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እርማት የሚደረገው የመታወቂያ ካርዱ ባለቤት የሚፈለገውን እርማት ጠቅሶ ሲያመለክትና እርማቱን ማድረግ ስለማስፈለጉ አሳማኝ ምክንያት በበቂ የሰነድ ማስረጃ ተደግፎ ሲቀርብ  ነው።
 • የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያው እንዲታረም ጥያቄ የቀረበው በመጀመሪያ መታወቂያ ከሰጠው አካል ውጭ ከሆነ እንደአስፈላጊነቱ ጥያቄው የቀረበለት የኢትዮጵያ ሚሲዮን ወይም ኢሚግሬሽን የእርማት ጥያቄውን ከማስተናገዱ በፊት መጀመሪያ የሰጠውን አካል በእርማቱ ጥያቄ ላይ ያለውን አስተያየት መጠየቅ ይኖርበታል።
 • እርማቱ የስም ለውጥ ከሆነ ስልጣን ከተሠጠው ፍርድ ቤት የተሰጠ እና አግባብ ባለው አካል በአሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ወይም በጋብቻ ምክንያት የስም ለውጥ ከሆነ አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የጋብቻ ማስረጃ እና ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሀላ ሰነድ ሁለት ቅጅ እንዲሁም የስም ለውጥ በጉዲፈቻነት ከሆነ አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ሕጋዊ የሰነድ ማስረጃ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
 • መታወቂያ ካርዱ መያዝ ያለባቸው መረጃዎችን አስመልክቶ የሚደረግ እርማት አሳማኝ በሆነ ምክንያት በሰነድ ማስረጃ ተደግፎ ሲቀርብ ለእያንዳንዱ የመረጃ ለውጥ ጥያቄ ከሁለት ጊዜ በላይ ከሆነ በሚሲዮኑ መሪ ወይም በኢሚግሬሽን ዳይሬክተር የሚወሰን ይሆናል።
 • እርማት የተጠየቀው በጋብቻ ምክንያት በተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆነ የውጭ አገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ የመታወቂያ ካርድ ላይ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ ሁለት ቅጅ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ ሊቀርብ ይገባል።
 • የእርማት አገልግሎት ከመወሰኑ በፊት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 10 ሥር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች የማይመለከቱት መሆኑ ሲረጋገጥና በእድሳት የክፍያ ተመን መሠረት ክፍያ ሲፈፀም ለአምስት ዓመት የሚያገለግል ተለዋጭ የመታወቂያ ካርድ ይሰጠዋል።
 • አሻራ ያልሰጡ ዕድሜአቸው 14 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው አመልካቾች ሁሉ አሻራ እንዲሰጡ ይደረጋል።
 • መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)
 • የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ
 • የተበላሸው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውና ሁለት ኮፒ
 • የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻር መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click here to download Fingerprint Capture FORM)
 • ሁለት (2) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)

የአገልግሎት ክፍያ

 •  ከ 18 አመት በላይ ለሆኑ 220 ዶላር፤
 • ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
 • መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም
 • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
 • አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ  የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL)ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ቅጾች /ፎርሞች/
 • በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነው ለመጀመሪያ ግዜ መታወቂያ ካርዱን ለሚጠይቁ/ቅጽ 1/ click here
 • በትውልድ ኢትየጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖራቸው ለባለቤታቸው ለሚጠይቁ/ቅጽ 2/  click here
 • መታወቂያ ካርዱ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ለሚጠይቁ  click here
 • በጠፋ ወይም በተበላሸ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ  Click Here
 • ሲጠቀሙበት የነበረ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለመመለስ ለሚጠይቁ /ቅጽ  click here
 • ከ18 ዓመት በላይ በውጭ ለተወሰዱ የውጭ ዜግነት ለያዙ ሰዎች፣