የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት

የውክልና እና የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ
እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ይላኩ።
  • እንዲረጋገጥልዎ የፈለጉት የውክልና ሥልጣን መስጫ ወይም የውክልና ሥልጣን መሻሪያ፣   የስምምነት ውል፣ ኑዛዜ፣ ቃለ ጉባኤ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የማህበራት መመስረቻ ጽሑፍ ወይም ሌላ ማንኛውም የሚረጋገጥ ሰነድ የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ያገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ካርድ(ቢጫ ካርድ) ወይም የአሜሪካ ፓስፖርት ወይም የማንኛውም ሌላ አገር ህጋዊ ፓስፖርት እና የአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ  እንዲረጋገጥልዎ ከሚፈልጉትን ውክልናው ወይም ማንኛውም የሚረጋገጥ ሰነድ ኦሪጅናል 3(ሶስት) ኮፒ  አስደርገው በቀጥታ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በአካል በመቀረብና በቆንስሉ ፊት በመፈረም አንዲረጋገጥልዎ ማድረግ ይችላሉ።  እንዲረጋገጥልዎ   የሚያቀርቡት የውክልና ወይም ሌላ ማናቸው ሰነድ 3 (ሶስት) ኮፒ የሆነው አንዱ ለቆንስላ ጽ/ቤቱ መዝገብ ቤት ቀሪ ተደርጎ ሁለቱ ተረጋግጦ ለእርስዎ ስለሚሰጥ ነው።
  • ነገር ግን በቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ   በአካል ቀርበው የውክልና ሥልጣን መስጫ ወይም የውክልና ሥልጣን መሻሪያ፣   የስምምነት ውል፣ ኑዛዜ፣ ቃለ ጉባኤ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የማህበራት መመስረቻ ጽሑፍ ወይም ዲክላራሲዮን ወይም ሌላ ማንኛውም  እንዲረጋገጥልዎ የሚፈልጉትን ሰነድ ማረጋገጥ ካልቻሉ ሰነዱን ኖትራይዝ አስደርገው በሚኖሩበት ግዛት  (your resident State) Secretary of State ወይም የግዛቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣  ቀጥሎ ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ሚገኘው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት(Department of State) ከተረጋገጠ በሁዋላ በፖስታ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በመላክ ሊረጋገጥልዎ ይችላል።
  • ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚቀርብ ዶክመንት ከአሜሪካን መንግስት የመነጨ (የተሰጠ) ከሆነ (ለምሳሌ የትምህርት ምስክር ወረቀት ወይም ዲፕሎማ፣ የሙያ የምስክር ወረቀት ወይም የወሳኝ ኩነት ሰነድ(የልደት ምስክር ወረቀት፣ የጋብቻ የምስክር ወረቀት፣ የፍቺ የምስክር ወረቀት፣ የሞት የምስክር ወረቀት) ወይም  ያላገቡ መሆንዎትን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የመንጃ ፈቃድ፣ እና የመሳሰሉትን  መጀመሪያ ካሉበት ግዛት ወይም Secretary of State ወይም የግዛቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣  ቀጥሎ ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ሚገኘው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት(Department of State) ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በፖስታ በመላክ ሊረጋገጥልዎ ይችላል።
  • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን
    ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ መደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት መደወል አይጠበቅብዎትም።
  • የውክልና ሥልጣን መስጫ ወይም የውክልና ሥልጣን  መሻሪያ፣   የስምምነት ውል፣ ኑዛዜ፣ ቃለ ጉባኤ፣ የመተዳደሪያ ደንብ፣ የማህበራት መመስረቻ ጽሑፍ ወይም ዲክላራሲዮን ወይም ሌላ ማንኛውም በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ ተጽፎ እንዲረጋገጥ የሚቀርብ ሰነድ በኮምፒተር፣ በ12 Font እና  1.5 Space መሆን አለበት።
  • የውክልና ሰነድ ናሙናዎች Click Here to Download, የጦረተኞች  Click Here to Download

 

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
 1

 

2

 ኖተራይዝ  የተደረገ የውክልና ሥልጣን መስጫ ወይም የውክልና ሥልጣን  መሻሪያ፣   የስምምነት ውል፣ ኑዛዜ፣ ቃለ ጉባኤ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የማህበራት መመስረቻ ጽሑፍ ወይም ዲክላራሲዮን ወይም ሌላ ማንኛውም የሚረጋገጥ ሰነድ ኖተራይዝ ከተደረገ በሚኖሩበት ግዛት  (your resident State) Secretary of State ወይም የግዛቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣  ቀጥሎ ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ሚገኘው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት(Department of State) ከተረጋገጠ በሁዋላ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በፖስታ መላክ፣የውክልና ሥልጣን መስጫ ወይም የውክልና ሥልጣን  መሻሪያ፣   የስምምነት ውል፣ ኑዛዜ፣ ቃለ ጉባኤ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ የማህበራት መመስረቻ ጽሑፍ ወይም ዲክላራሲዮን ወይም ሌላ ማንኛውም የሚረጋገጥ ሰነድ ኖተራይዝ ሳያስደርጉ ወደ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን  በአካል ቀርቦ ማስፈፃም ይችላሉ።
3 በአካል የሚቀርቡ ከሆነ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆኑ የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከነ ኮፒው ፤ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ የታደሰ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ ካርድ(ቢጫ ካርድ) ከነ ኮፒው ፣ አሜሪካዊ ከሆኑ የታደሰ የአሜሪካ ፓስፖርት ከነ ኮፒው  ወይም የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ የታደሰ የአገሩን ፓስፖርትከነ ኮፒው እና የአሜሪካ መኖሪያ ፈቃድ(Green Card) ከነ ኮፒው፣
 4  በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆኑ በአሜሪካን አገር የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የግሪን ካርድ ከነ ኮፒው  ወይም ግሪን ካርድ ከሌለዎት የ I – 94 ወይም የስራ ፍቃድ ማስረጃ ኮፒ
 5 የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያዊ ወይም ለትውልደ ኢትዮጵያዊ ለውክልና ሥልጣን መስጫና መሻሪያ ሰነድ $62.00 ዶላር እንዲሁም ለሌሎች ህጋዊ ሰነዶች(የትምህርት፣ የልደት፣ የጋብቻ፣ የመንጃ ፈቃድና የመሳሰሉ የምስክር ወረቀቶች)  ማረጋገጫ $59.00 ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/፣
6 የአገልግሎት ክፍያ ለአሜሪካዊ ወይም የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ለውክልና ሥልጣን መስጫና መሻሪያ ሰነድ $95 አንዲሁም ለሌሎች ህጋዊ ሰነዶች(የትምህርት፣ የልደት፣ የጋብቻ፣ የመንጃ ፈቃድና የመሳሰሉ የምስክር ወረቀቶች)  ማረጋገጫ $90.00 ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/
 7 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (Click here to download a Form)
8  በፖስታ የሚልኩ ከሆነ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
ማሳሰቢያ v በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

 

. በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 መጀመሪያ ለማረጋገጥ የሚፈለገው ዶክመንት በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል
2 የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ ሆኖ የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ  ኮፒ ካያያዙ $59.00 ዶላር ሲሆን የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት የፍርድ ቤት ውሳኔዎችና ሀብት ነክ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ሰነዶች/ውክልና $95.00 ዶላር፣ የትምህርት፣ የልደት፣ የጋብቻ፣ የመንጃ ፈቃድና የመሳሰሉ የምስክር ወረቀቶች $90.00
ነው፡፡
3 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download a form)
4 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
አገልግሎቱ የሚፈጅበት ጊዜ
  • በአካል ቀርበው ለሚያስፈፅሙ በ2o  ደቂቃ ውስጥ፣
ለሁሉም ዶኩመንት ለማረጋገጥ
  • በመልዕክት /mail/ ለሚልኩ ማመልከቻው ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ በ48ሰዓት ተጠናቅቆ ይላካል፣
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ቅጾች /ፎርሞች/
1.      የማመልከቻ ቅጽ   (click here to download a form)