የሊሴ ፓሴ አገልግሎት

LAISSEZ PASSER

1.  የአንድ ጊዜ የጉዞ ሰነድ/ ሊሴ ፓሴ ለማመልከት
 • የአገልግሎት ግዜውን ያበቃ ፓስፖርትዎ ለማሳደስ በቂ ጊዜ ከሌለዎትና በተለያየ አስቸኳይ ምክንያት ወደ አገርቤት ለመጓዝ ከፈለጉ ሌሴ ፓሴ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • ሊሴ ፓሴው ለአንድ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ ፓስፖርት ማውጣት እንዳለብዎ አይዘንጉ፡፡
 • የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከቆንስላ ጄኔራሉ ጽ/ቤት ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ የጉዞዎ ቀን ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ የከፈሉበትን ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን መረከብ ይችላሉ።
የፖስታ አላላክ መመሪያ

 • በፖስታ ቤት አማካኝነት ሊሴ ፓሴ የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL) መሆን ይገባዋል፡፡
 • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎ ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡
 • የሊሴ ፓሴዎ ማመልከቻ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ከተረከበት ከሁለት ወይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ!
  ማሳሰቢያ፡-
  • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
 • ሁለት (2)  የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
 • አገልግሎቱ ያበቃዉን ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ኮፒ ማቅረብ
 •  ፓስፖርትዎ ከጠፋ የትና መቼ እንደወሰዱት የሚገልጽ ማስታወሻ እንዱሁም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ
 • በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ
 • የግሪን ካርድ  ወይም
 • ግሪን ካርድ ከሌለዎት የ i-94 ወይም የስራ ፍቃድ ኮፒ ማያያዝ
 • የአገልግሎት ክፍያ $50.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/
 • የሊሴ ፓሴው ማመልከቻ በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ የግላችሁን አድራሻ Tracking Number ባለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL)  ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
ማሳሰቢያ፡-
 • በFEDEX የመመለሻ ፖስታ አገልግሎት የምትጠቀሙ ከሆነ የFEDEX አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል። ሆኖም ግን የFEDEX አካውንት ከሌላችሁ ጥያቄያችሁን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
 • ፓስፖርቱ ስለመጥፋቱ የሚገልጽ የፖሊስ ማስረጃ ያስፈልጋል፣