Citizen Charter

የሎስ አንጀለስ ኢፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር ይዘት


 1.   የቻርተሩ ዓላማ

 • የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ማረጋረጥ፤
 • ለዜጎች ጥራት ያለው አገልግሎት ለመሰጠት፤
 • ተጠያቂነትን በግልጽ ለማመልከት፤
 • ዜጎች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ፍጥነት፣ በምን የጥራት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፤

2.   የጽ/ቤቱ ራዕይ

 • በበጀት ዓመቱ ከትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እና ሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን አገራችን ከአሜሪካ አገር ጋር ያላትን የቢዝነስና የኢኮኖሚ ግንኙነት ለማጠናከርና ለዜጎቹ የላቀ የኮንስለር አገልግሎት የሚሰጥ ጽ/ቤት መሆን፣

3.   የጽ/ቤቱ ተልእኮ

 • “ቀጣይና አሰተማማኝ ተቋማዊ የለውጥ ስርዓት በመዘርጋት፤ የልማት ትግላችንን የሚያሳካ፤ የሰላም ስጋቶችን የሚያስወግድና ለልማት የተመቻች ሁኔታን የሚፈጥር፤ መልካም ገጽታን የሚገነባ፤ የዲያስፖራ ተሳትፎን የሚያሳድግና ጥቅምን የሚስጠብቅ ዲፕሎማሲ ማራመድ”

4.   የጽ/ቤቱ ዕሴቶች

 • የሕዝብ አገልጋይነት –  Public Service
 • አጋርነት – Partnership
 • ተዓማኒነት – Integrity
 • ቁርጠኝነት – Commitment
 • ግልጸኝነት – Transparency
 • ውጤታማነት – Effectiveness ናቸው።

5.   የእሴቶች መግለጫ


5.1.  የሕዝብ አገልጋይነት (Pbblic Service)

 •   ዜጎቻችንና ባለድርሻ አካላትን በከፍተኛ ትህትና፡ ቅንነትና ቅልጥፍና ማገልገል ኃላፊነታችንና ግድታችን ነው። ይህም በየዕለቱ በምናደርገው ዲፕሎማሲያዊ ተግባራችን ይገለፃል። ይህ እሴታችን ደንበኞቻችንና ተጠቃሚዎች በምናስገኘው የእርካታ መጠን፤ እንዲሁም እያንዳንዱን አገልግሎት ለመሰጠት ከወሰድነው ጊዜና ጥራት አንፃር የሚለካና በዕለት ተዕለት እንቅስቃስያችን ውሰጥ ተግናራዊ የሚደረግ ይሆናል።

     5.2.  አጋርነት (Partnership)

 • እንደተቋምና እንደግለሰብ የመ/ቤቱን ተልዕኮና ራዕይ በተሳካ ሁኔታ ተግማራዊ ለማድረግ የተቋሙ ሠራተኞች እርስ በርሳችን፤ እንዲሁም ከልሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ሰካላትና የልማት ጋሮች ጋር በምንፈጥረው ወዳጅትና የተቀናጅ አሰራር አጋርነትን እናጎለብታለን። አጋርነት የዕለት ተዕለት ሥራችን መገለጫ ሲሆን ይህም የመ/ቤቱን ራዕይ እና ተልዕኮ በማሳካት ሂደት ባፈራናቸው አጋሮች ብዛት የሚለካ ዕሴት ነው።

5.3.   ተዓማኒነት (Integrity)

 • ለመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራትጂዎች ጥብቅና በመቆም በታማኝነትና በቁርጠኝነት መፈፀም፤ የሀገርንና የዝባችን ጥቅም በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ማሰጠነቅ እንዲሁም የአገርንና የተቋሙን ምስጢሮች መጠበቅ፤ ከአድልዎ የፀዳ ግልጽ አሠራር መዘርጋት፤ ፍትሐዊነት፤ ቅንነት፤ ግልጽነትና ተጠታቂነትን በሚያረጋግጥ አኳኃን የተቋሙን ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃትና ውጤታማነት መወጣትን ይመለከታል። ይህም ይተቋሙን የሥራ ዕቅዶችና ግቦችን ከመተግበርና ከማሳካት አኳያ የሚለካ ይሆናል፡

       5.4.   ቁርጠኝነት

 •  ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ፤ ኪሞከራሲዊ ሰረዓት ለመገንባትና የአገራችንን ደህንነትና ሠላም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መነሳሳት ወሣኝ ነው። በመሆኑም ተቋማዊ ኃላፊነታችንን ለመግለጽ በየደረጃ ለሚካሄድ የዲፕሎማሲ ሥራ ቁርጠኛ አቋም መያዝ ከሁሉም የሚጠበቅ እሴት ነው።

       5.5.     ውጥታማነት (Effectiveness)


 • የዲፕሎማሲ ሥራችንንና አሰልግሎት አሰጣጣችን በቅልጥፍና ከመስራት በሻገር ሥራዎቻችንና አገልግሎቶቻችን ጥቅም የሚሰጡና ውጤት የሚያስመዘግቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

6.   ተገልጋዮች

 • የውጭ ዜጎች፤
 • የውስጥ ሠራተኞች፣
 • በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊናንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤
 • በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋሙ የኢትዮጵያ ህዳሴ ምክር ቤቶች፣ የልማት፤ የሙያ፤ የቢዝነስና ሌሎች ማህበራት፤
 • በውጭ ያሉ የሃይማኖት ድርጅቶች
 • የኢትጵያውን የተያዙ ቱር ኦፕሬተሮች፤

7.  አጠቃላይ መርሆዎች

 • ቀልጣፋ፤ ጥራት ያለው ፤ ውጤታማና አስተማማኝ የመረጃ አገልግሎት እንሰጣለን፤
 • ቀልጣፋ፤ ጥራት ያለውና ውጤታማ፤ የፓሰወፖርትና ቪዛ፤ የሠነድ ማረጋገጥና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ፈጣን የፕሮቶኮል አገልግሎት እንሰጣለን፤
 • ላሰቀመጥናቸው እሴቶች እንገዛለን፤
 • ለዜጎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ፈጣን መልስ እንሰጣለን፤
 • ከአድሏዊ አሰራርና ከሥነ-ምግናር ጉድለት የፀዳ አሰራርን እንከትላለን፤
 • ለሰጠናቸው አገልግሎቶችና ለወሰናቸው ዉሳኔዎች ተጠያቂዎች ነን፤

8.   የተገልጋዮች መብቶች

 • በጽ/ቤቱ የሚሰጡትን አሰልግሎቶች የመጠየቅና የማገኘት፤
 • የተሟላ መረጃ የማግኘት፤
 • በፍጥነትና በቅልጥፍና የመሰተናገድ፤
 • የተሰጣቸውን አገልግሎት በተመለከተ አስተያየት የመሰጠት፤
 • ባልተገናኘ አገልግሎት ቅሬታዎቻቸውን በየደረጃው የማሰማትና ለቅሬታዎቻቸው ምላሽ የማግኘት፤

9.  ከተገልጋዮች የሚጠበቅ ግድታ

 • ትክክለኛና ታማኝነት የሆነ መረጃ አሟልቶ ማቅረብ፡
 • ታማኝነት፤
 • በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አሰተያየት መሰጠት፤

10.   ከጽ/ቤት የሚጠበቁ ስኬቶች (Outcomes)

 • የተፈጠረ ጠንካራ የዳያሰፖራ ትስስር፤
 • በቢዚነስ ፍሰት የተገኘ ተጨማሪ የውጭ ሀብት፤
 • ለልማት፤ ሰላምና ኪሞድራሲ ስረዓት ግንባታ የተመቻቸ የውጭ ሁኔታ፤
 • የተገነባ የሀገር ገጽታና የተበራከቱ ደጋፊዎች፤
 • የተደረገ የትክኖሎጂ ሽግግር
ተ.ቁ የሚሰጡ አገልግሎቶች አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ የአገልገሎት አሰጣጥ ሰታንደርድ አገልግሎቱን ለማገኘት የሚጠየቅ ቅድመ ሁኔታ
ጊዜ ጥራት ብዛት

ሀ. በፖለቲካና ኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ የሥራ ዘርፍ የሚሠጡ አገልግሎቶች

1 የአፍሪካ ቀንድ ትንተና  A week in the Horn መለጠፍ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና  ኢኮኖሚክ ዲፐሎማሲ በ2 ሳምንት አንድ ቀን በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ታይቶ እና ተገምግሞ የሚቀረብ፤ የተላከው ·         ኢንተርኔት መጠቀም
2 ኢትዮጵያ ነክ ዜናዎችንና መረጃዎችን በመጫን በድህረ-ገጾች ላይ በመጫን ለተደራሾች እንዲደርስ ማድረግ፤ ዳያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ በየቀኑ በዋናው መ/ቤት የሚቀርብ የተላከው ·         ኢንተርኔት መጠቀም
3 የአገራችንን እምቅ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ሀብት የሚያሳይና የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ሊስቡ የሚችሉ ወቅታዊ፣ ወጥነትና ጥራት ያላቸዉ የፕሮሞሽን መረጃዎችን ማቅረብ፤ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና  ኢኮኖሚክ ዲፐሎማሲ በስድስት ወር በመ/ቤቱ ዋና ክፍል የሚላክ፤ የተገኘው ·         የተዘጋጀው ዶክሜንት በ CD ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዳሴ ምክር ቤቶችና ለተደራሾች እንዲደርስ ይደረጋል
4 ከተሞችን ክልሎችን፤ የትምህርት ተቋማትንና ከአቻ ተቋማት ጋር ለማጎዳኘት የሚሰፈልጉ መረጃ ልውውጦችን ማካሄድ፤ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና  ኢኮኖሚክ ዲፐሎማሲ በአንድ ወር በዳ/ጄኔራሉ  የሚላክ፤ የተገኘው የተጓዳኙን ተቋም/ድርጅት ፐሮፋይል ማቅረብ፤
ለ. በቢዝነስና ኢኮኖሚ ማሰፋፊ የስራ ዘርፍ የሚሠጡ አገልግሎቶች፤
1 ለወጪ ምርቶቻችን አዳዲስ ገበያ ማፈላለግ፤ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ዘርፍ በአንድ ወር በጹሁፍ ማቅረብ የተገኘው ምርቱን የሚገልጽ የተሟላ መረጃና ገበያ ሚፈለግለትን አገሮች (አገር) በመግለጽ ጥያቄውን በደብዳቤ ማቅረብ፤
2 በቢዝነስ ስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ማነቆዎች መፍትሔ እንዲገኙ ማድረግ፤ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ዘርፍ በ30 የስራ ቀናት  በጽሑፍ በማቀረብ የተገኘውን ·         ችግር የደረሰነት ድርጅት (ኩባንያ) ሙሉ ስም፤ አድራሻ የተሰማራበት የስራ አይነት፣ ያጋጠመውን ችግር እና የመፍትሄ ሃሳብ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቀረብ፤
3 በሚሲዮን ደረጃ ገዢዎችን  አፈላልጎ በማግኘት መረጃውን ወደ ዋናው መ/ቤት መላክ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ዘርፍ 2 ወር በጽሁፍ የተገኘውን በኢ-ሜይልና በፓዉች
4 በተለያዩ የቢዝነስ ኤግዚቢሺኖችና የንግድ ትርኢቶች ላይ ለሚደረግ ተሳተፎና ሌሎቸች የፕሮሞሽን ሥራዎች ድጋፍ መሰጠት ፖለቲካ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ዘርፍ እንደ ፕሮገራሙ ዝግጅት ስፋት በጽሑፍ 2 o   የኤግዚብሸን አይነት፤ የሚያካሄዱበት ቦታ፤ ጊዜ ወዘተ… ዝርዝር መረጃ ማቅረብ
5 የውጭ የቱር ኦፕሬተሮች በአገራችን ለሚደርጉት ጉብኝት አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት፤ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ዘርፍ 1 ቀን በጽሑፍ

በግምባር

የቀረቡትን የኩባንያውን (የድርጅቱ) የተሟላ ፕሮፋይልና ፐሮፖኣል ከደብዳቤ ጋር ማቅረብ
6 አገራችን ለምትፈልገው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት ድጋፍ ማድረግ፤ ፖለቲካ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ዘርፍ 1 ቀን በጽሑፍ

በግምባር

የቀረቡትን የጥያቄ አቅራቢው መስሪያ ቤት (ድርጅት) ፕሮፋይልና Contact Person፤
7 የቢዝነስ (የንግድ፤ የኢንቨስትመንት፤ የቱሪዝም እና የመሠረተ ልማትና የቴክኖሎጁ ሽግግር ወዘተ) መሰረታዊ መረጃዎችን መሰጠት ፖለቲካ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ዘርፍ በሥራ ክፍሉ የሚገኝ መረጃ በ 1 ቀን በኢሜይል

በፋክስ

የተጠየቀው በኢ-ሜይል፤ በስልክ፤ በአካልና ደብዳቤ መጠየቅ፤
ሐ. በዲያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች የሥራ ዘርፍ የሚሠጡ አገልግሎቶች፤
1 ከኢንቨስትመንት ተሳትፎ ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች የድጋፍ ደብዳቤ መሰጠት፤ ዲያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ በ30 ደቂቃ የተሟላ መረጃ የተጠየቀው ለኢትዮጵያዊያን በውጭ አገር የመኖሪያ ፈቃድና የፀና የውጭ አገር ኦርጅናል ፓስፖርትና ፎቶ ኮፒ፤

ለትውልድ ኢትዮጵያዊያን አገልግሎት የፀና የውጭ አገር ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ፤

2 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በኢንስትመንት ተሳትፎ እንቅስቃሲያቸው፣ በቤትና ቦታ ይዞታና መሰል ጉዳዮች ማነቆዎች ሲገጥማቸው የየድጋፍ ደብዳቤ መጻፍ፣ ዲያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ በ1 ሰዓት በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው ·         የፕሮጄክታቸውን/ድርጅታቸውን ፎቶ ኮፒ፣

·         የፓስፖርታቸውን ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ እና ማመልከቻ

 

3 በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ከተለያዩ የአገር ውስጥ ተቋማት ጋር ግንኙነትና ድጋፍ ማደረግ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤ ዲያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ ከ 1-10 ቀናት በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው ·         በአካል፤ በደብዳቤና በልሎች አመቺ የግንኙነት ዘዴዎች የሚቀርብ የድጋፍ ጥያቄ፤

 

4 በኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በአገር ውስጥ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሣብ እንዲከፍቱ የመረጃ አገልግሎት መስጠት፤ ዲያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ በ30 ደቂቃ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው ·         በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆን፤

·         በትክክል የተሞላና በሂሳብ ከፋቹ የተፈረመ የማመልከቻ ፎረም፤

5 ለታላቁ ሕዳሌ ግድብ ማስጨረሻ ገቢ የማሰባሰብ አገልግሎት መስጠት፤ ዲያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ በ1 ወር በተቻለ ፍጥነት፤ የተጠየቀው ለኢትዮጵያንና  ለኢትዮጵያውያን ወዳጆችና  Pledge  form  ማቅረብ፣
መ. መንግስታዊ ያልሆኑ ስራዎች/ NGO ነክ
1 በውጭ አገር የተመሰረቱ ዓለምአቀፍ መንግሥታዊ ያለሆኑ ድርጅቶች በአገራችን ውስጥ ተመዝግቦ ለመሥራት የሚያቀረቡትን ጥያቄ በማጣራት ለበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ምዝገባ ኤጀንሲ የድጋፍ ደብዳቤ መፃፍ፤ ፖለቲካና ፐብሊክ ዲፕሎማሲ በ1 ሰዓት በተቻለ ፍጥነት፤ የተጠየቀው o   የበጎ አድራጎት ድርጅት መቋቋሙን የሚያሳይ  በተቋቋመበት  አገር የተሰጠውን  የተረጋገጠ  ሰነድ የምስክር  ወረቀትና  ማመልከቻ፤

 

ሠ. የኮንሱላር አገልግሎቶች የሥራ ዘርፍ የሚሠጡ አገልግሎትች፤
1 አዲስ ፓስፖርት፣ የኮንሱላር ወይም ኢሚግሬሽን ክፍል ከ30 – 50 ደቂቃ

 

በመመሪያው መሰረት ሆኖ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው o   አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ ያስፈልግዎትም፡፡

o   እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀደም ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዲሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14 ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2  ፓስፖርት እድሳት፣

 

የኮንሱላር ወይም ኢሚግሬሽን ክፍል ከ30 – 50 ደቂቃ

 

በመመሪያው መሰረት ሆኖ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው
o   4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
o   ለመቀየር ወይም ለማሳደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ
o   ለመቀየር ወይም ለማሳደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ
o   በአሜሪካን አገር የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ  የግሪን ካርድ  ወይም ግሪን ካርድ ከሌለዎት i-94 ኮፒ ወይም የስራ ፍቃድ ማስረጃ  በሁለት ኮፒ
3  በጠፋ ፓሰፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት የኮንሱላር ወይም ኢሚግሬሽን ክፍል ከ30 – 50 ደቂቃ

 

በመመሪያው መሰረት ሆኖ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው
o   4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
o   የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ  በሁለት  ኮፒ  ማቅረብ
o   በአሜሪካን አገር የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ  የግሪን ካርድ  ወይም ግሪን ካርድ ከሌለዎት የ i-94 ኮፒ ወይም የስራ ፍቃድ  ማስረጃ   በሁለት ኮፒ
4 የአንድ ጊዜ የጉዞ ሰነድ/ ሊሴ ፓሴ ለማመልከት የኮንሱላር ወይም ኢሚግሬሽን ክፍል ከ30 – 50 ደቂቃ

 

በመመሪያው መሰረት ሆኖ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው
o   ሁለት (2)  የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
o   አገልግሎቱ ያበቃዉን ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ኮፒ ማቅረብ
o   ፓስፖርትዎ ከጠፋ የትና መቼ እንደወሰዱት የሚገልጽ ማስታወሻ እንዱሁም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ
o   በአሜሪካን አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ ኮፒ
o   የግሪን ካርድ  ወይም

o   ግሪን ካርድ ከሌለዎት የ i-94 ወይም የስራ ፍቃድ ኮፒ ማያያዝ

5  የኢትዮጵጵያ ተወላጅነት መታወቂ ካርድ ለማግኘት የኮንሱላር ወይም ኢሚግሬሽን ክፍል ከ30 – 50 ደቂቃ

 

በመመሪያው መሰረት ሆኖ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው o   የአመልካቹ አግባብ ካለው አካል የተሰጠና የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር፣ ወይም፣

o    የአመልካቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር  ወይም፣

o   ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ ከነበሩ የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ፣ ወይም፣

o   ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋግጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉድፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ፣ ዋናውን ከሁለት ቅጅዎች ጋር ፣ ወይም፣ ስልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠ እና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ ፣ ወይም፣

o   ሥልጣን ካለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም አያቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ

6 በውጭ አገር አድራሻቸው የጠፉ በጉድፈቻ የመጡ ኢትዮጵያውያን ህጻናትን ከቤተሰቦቻቸው  ጥያቄ ሲቀርብ ለሚመለከተው አጣርቶ ማሰተላለፍ፤ የሰነድ ማረጋገጥ፣ አሻራና ውክልና አገልግሎት ክፍል፣ 40 ደቂቃ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው ለመቀየር ወይም ለማሳደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ
7 ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከውጭ አገር ጓዛቸውን ጠቅልለው ሲመለሱ የመገልገያ ዕቃዎቻቸውን ቀረጥና ታክስ ከፍለው እንዲያሰገቡ አስፈላጊና ህጋዊ ድጋፍ መስጠት የሰነድ ማረጋገጥ፣ አሻራና ውክልና አገልግሎት ክፍል፣ 40 ደቂቃ በመመሪያው መሰረት ሆኖ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው o   እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡

o   አምስት አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርቦታል

o   በአምስት አመት ውስጥ ከአንድ ግዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም

8 የተለያዩ ሰነዶችን ማረጋገጥ፤ የሰነድ ማረጋገጥ፣ አሻራና ውክልና አገልግሎት ክፍል፣ ከ30 – 50 ደቂቃ

 

በመመሪያው መሰረት ሆኖ በተቻለ ፍጠነት፤ የተጠየቀው o   ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚመጣው ዶኩመንት ከአሜሪካን መንግስት የመነጨ ከሆነ (ለምሳሌ – ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣  የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ካሉበት አካባቢ ወደሚገኘው ስቴት ኦፊስ በመሄድ ዶኩመንቱን ካረጋገጡ በኋላ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው Secratory of State ተረጋግጦ ወደ እኛ መምጣት አለበት፡፡

o   ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደኛ በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ

የቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ ተጨማሪ መረጃዎች

 

 • አድራሻ፡-Consulate General of Ethiopia
 • Wilshire Boulevard #1101.

Los Angeles, California 90010

1.  የቅሬታ አቀራረብ ሂደት

 

 • ወደ ጎን
 • ቅሬታን አገልግሎት ለሰጠው አካል በቀጥታ፤
 • ለቅረብ የስራ ኃላፊ፤
 • ለሥራ ከፍሉ የበላይ ኃላፊ፤
 • ወደ መ/ቤቱ የቅሬታ ክፍል በግንባር በመቅረብ፤
 • ለመ/ቤቱ የበላይ አመራር አካላት፤
 • በሚሰጠው ምላሽ ያልረካ ተገልጋይ በየረደጃው ለሚገኙ አካላት ቅሬታውን ማቀረብ ይችላል
 • በስልክ፣ በዌብሳይት፤ በኢ-ሜይል እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ፤

2.    የክትትልና ግምገማ ሥርዓት

 • በBSC ደረጃ 9 መሠረት የውጤት ተኮር ዕቅድና በጀት አዘገጃጀት፤ የአፈፃፀም መረጃ አደባሰብ፤ ክትትል፤ ግምገማና ምዝና መመሪያ መሠረት፤
 • ሳምንታዊ፤ ወርሃዎ፤ የሩብ ዓመት፤ የ6 ወር፤ የ9 ወርና ዓመታዊ ሪፖርቶች ቀርበው ይገምገማሉ፡፡ የሚሰጡ ግብረ መልሎችን እንደ ግብአት በመጠቀም፤
 • በቻርተሩ ላይ በተቀመጠው መሠረት፤
 • የተገልጋዮች እርካታ ሰርቬይ በማካሄድ፤

ለፊርማ ማረጋገጫ በተገልጋዮች የሚከፈል የአገልግሎት ዋጋ

ተ.ቁ የአገልግሎት ዓይነት የአግልግሎት ዋጋ /በአሜሪካ ዶላር
ለኢትዮጵያኖች ለውጭ ዜጎች
1 የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ / የትምህርት፤ የልደት፤ የጋብቻ፤ የመንጃ ፈቃድና የመሳሰሉት የመስክር ወረቀቶች 59 95
2 አዲስ ፓስፖርት 60
3 በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት መቀየር 90
4 አገልግሎቱ ያለቀበት ፓስፖርት ማደስ 60
5 የአንድ ጊዜ የጉዞ ሰነድ /ሊሴ ፓሴ 50
6 የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂ ካርድ 200
7 ጠቅልለው ወደ አገር ቤት የሚገቡ ዜጎች
8 የውክልና አገልግሎቶች 62 95
9 ለቱሪስት ቪዛ 70
12 ከአሜሪካ ዜግነት ውጭ ላሉት ሌሎች የውጭ ዜጎች    
 12.1 ለ30 ቀን ለአንድ ጊዜ / Single Visa / 40 USD
 12.2 ለ3 ወር ለአንድ ጊዜ / Single Visa / 60 USD
 12.3 ለ3 ወር የብዙ ጊዜ መመላለሻ 70 USD
  2.4 ለ6 ወር የብዙ ጊዜ መመላለሻ 80 USD

 

13 የስራ  ቪዛዎች የቪዛው ዓይነት ለአንድ ጊዜ እስከ 1 ወር ለ3 ወር 1 ጊዜ ለ3 ወር የብዙ ጊዜ ለ6 ወር የብዙ ጊዜ 1 አመት የብዙ ጊዜ
 13.1 ለኢንቬስትመንት (ለንግድ ስራ) I-V 30 USD 40 USD 60 USD 120 USD
 13.2 ለተለያዩ መንግስታዊ ለሆኑ ስራዎች G.I.V 20 USD 80 USD 120 USD
 13.3 ለውጭ ባለሀብት ተቀጣሪለመንግስት W-V 40 USD 60 USD 80 USD
 13.4 ለመስሪያ ቤት ተቀጣሪ G-V 30 USD 40 USD 60 USD
 13.5 ለመንግስታዊ ላልሆኑ መያዶች (NGO ) N-V 60 USD
 13.6 ለአህጉራዊና አለም አቀፍ ድርጅት ተቀጣሪ R-I 50 USD 70 USD 90 USD
 13.7 ለአጭር ስብሰባ ፣ ለወርክሾፕ፣ ለአውደ ጥናት C-V 30 USD
 13.8 ለሚዲያ  (ጋዜጠኛ) J-V 40 USD
 13.9 ለግል ድርጅት ተቀጣሪ P-E 30 USD 50 USD 80 USD